የኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ፤ ርዕይና ዕሴቶች
የኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ
የክልሉን የዳኝነትና የፍትህ አካላት ቀልጣፋ ፣ ዉጤታማ፣ ተደራሽ፣ ገለልተኛ እና የህዝብ አመኔታን ያተረፉና እርካታን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ፤ የዳኝነትና የፍትህ ዘርፉን አመራሮችና ባለሙያዎች በዕዉቀት፣ በክህሎት እና በሥነ-ምግባር በማነፅ ዘርፉ ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት እና ሥነ-ምግባር ባላቸዉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲገነባ በማስቻል፣ በጥናትና ምርምር ዉጤት ላይ የተመሰረተ ፣ የተተነተነ የፍትህ አስተዳደር ሥርዓት መረጃ ማዕከል በማበልፀግ፤ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የሥልጠናና የጥናትና ምርምር የልህቀት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ርዕይ
- በ2022 ዓ.ም ለፍትህና የሕግ የልሕቀት ማዕከልነት የሚያበቁ የተቋም ግንባታ ሥርዓት መሠረቶች ዕውን ሆነው ማየት!
- በ2027 ዓ.ም ቴክኖሎጂ መር ውጤታማ የፍትህና የሕግ የልሕቀት ማዕከል ሆኖ ማየት!
- በ2042 ዓ.ም በአፍሪካ ተምሳሌት የሆነ የፍትህና የሕግ የልሕቀት ማዕከል ሆኖ ማየት!
የኢንስቲትዩቱ ዕሴቶች
ኢንስቲትዩቱ በሕግ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት በመወጣት ተልዕኮንና ርዕይን ለማሳካት በሚከተሉት ዕሴቶች ይመራል፡፡
- ለፍትህና ለሕግ ልህቀትነት መትጋት!
- ተቋማዊ ነፃነት፤ ገለልተኝነትና ተጠያቂነት!
- ሙያዊ ብቃትና ፈጠራ!
- ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት!
- ሥትራቴጂካዊ አጋርነትና ቅንጅታዊ አሠራር!
- አሳታፊ አመራር ሰጭነትና ታማኝነት!
- ሥነ-ምግባራዊ ምሳሌነት!
- የለውጥ አስቀጣይነት!
