የህግ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ለአውደ ጥናት ቀረቡ
የአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና ህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ሁለት የህግ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለዓውደ ጥናት አቀረበ በዚህ ዓውደ ጥናት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ አፈ_ጉባኤ ክብርት
ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ እንደገለጹት በአገራችን ብሎም በክልላችን እየታየ ያለውን የፍትህ መጓደል ና ህዝቡ የሚጠይቀውን አገልግሎት አለማግኘት ችግሮች ለመፍታት ና የተጀመረውን የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ሥራ ጥራትና ፍጥነት ለመጨመር ፤ ሳይንሳዊ የሆኑ የህግ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ድርሻ ትልቅ ነው።
በመሆኑም እየታዩ ያሉትን ስብራቶች ለመጠገን ትልቅ ሃቅም ናቸው። የጥናት ስራዎቹ “የፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር በአማራ ክልል” እና “
“የገንዘብ ቅጣት አወሳሰን ና አፈጻጸም በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች” በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች የተጠኑ ናቸዉ ። በዚህ ዐውደ ጥናት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አቡየ ካሳሁን ፣የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሹ፣ የክልሉ ህግና ፍትህ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ደሴ ጥላሁን ና ከየሚመለከታቸው ተቋማት ጥሪ የተደረገላቸው የህግ ሙሁራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ አበራ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በአጫጭር ፣በመካከለኛ ና በቅድመ ሥራ ሥልጠናዎች እንዲሁም የተሠሩ የጥናት ና ምርምር ሥራዎችን አጭር መረጃ ለተሳታፊዎች በመስጠት ተቋሙ የራሱን ሚና እየተወጣ መሆኑን አስረድተዋል ።
በዚህ መድረክ የመጀመሪያው የጥናት ስራ “የፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር በአማራ ክልል” በሚል በአቶ ይማም ሰይድ የተጠናው ሥራ ለተሳታፊዎች ቀርቦ በዶ/ር አያሌው አባተ እና በኢንስቲትዩቱ የህግ ጥናት ናምርምር የስራ ሂደት መሪ አቶ አበበ ካሴ አወያይነት ሰፊ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በዚህም የተፈለገውን ያህል ግብዓት እየተገኘ ነው።
