የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት “ጁሪስ ሰርክል (Juris Circle)” ሙያዊ የውይይት ማዕቀፍ አሠራር ሥራ ጀመረ!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት “ጁሪስ ሰርክል (Juris Circle)” ሙያዊ የውይይት ማዕቀፍ አሠራር ሥራ ጀመረ!

ኢንስቲትዩቱ ሥራ ያስጀመረው የአሰራር ማዕቀፍ Juris Circle of Justice & Law Institute (JCJLI) ይሰኛል፡፡ የፍትሕና የሕግ የልህቀት ማዕከልነትን ይበልጥ ለማጠናከር የአብክመ የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችና አመራሮችን የያዘ፤ በህግ ፍልስፍና፤ በወቅታዊ የህግ ጉዳዮች፤ በዘርፉ ተቋማትና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፤ የጉዳዮች ላይ ውይይት፤ የጥናትና ምርምር ጭብጦች፤ ከዘርፉ አንፃር ብሔራዊ ጥቅምን በሚመለከቱ እና መሠል ጉዳዮች ጥልቅ መማማር እና የዕውቀት ክምችት ሥራን ዛሬ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ተንተርሶ በይፋ ተጅምሯል፡፡ JCJLI የሚመራበት አሠራር በውይይት ዳብሮ ፀድቋል፡፡

በሚከተሉት ርዕሠ ጉዳዮች ላይም የአመራርና ባለሙያ ምደባ፤ የጭብጥ ልየታ ሥራ እና ዝርዝር አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡ ርዕሠ ጉዳዮቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

– The Sovereign Right to Access to the Sea under International Law: Contemporary Quest of Ethiopia and its Legal, Economic, and Historical Ties

– Recognition of States under International Law: The Recent Trends and its political and Legal Implications

– Government-Organized Non-Governmental Organizations (GONGOs): Global Experience and their Legal Regime

በርዕሠ ጉዳዮቹ ላይ በተሰሩ ጥናታዊ ሥራዎች ውይይት የሚደረግባቸው ጊዚያት የተወሰነ ሲሆን በቀጣይም፤ በግኝቶች እና በተደረሰባቸው መግባባት ላይ ለተከታታዮች መረጃዎችን በተለያዩ ዘዴዎች ተደራሽ የሚደረጉ ይሆናል፡፡ የሙያዊ ውይይቱን ተሳታፊዎች አድማስ ለማስፋት በቀጣይ ከዘርፉ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በጋራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

መልካም የፈረንጆች አዲስ ዓመት!

January 1, 2026

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top