የአብክመ የፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት ለአስራ ሰባተኛ ጊዜ ለተቀበላቸው የቅድመ ስራ ሰልጣኞች ምዘና ሰጠ
ኢንስቲትዩቱ በገጽ ለገጽ ሲሰጥ በነበረው የሥልጠና ቆይታ ያስጨበጠውን እውቀት ለመለካት የሚያስችል የሙያ እና የስነ-ምግባር መመዘኛ ፈተና አዘጋጅቶ ፈትኗል።
ከሰልጣኞች መካከል ወጣት ጀማል ውዴ ለኢንስቲትዩቱ ህዝብ ግንኙነት እንደገለጸው ምዘናው ማስተዋልን ና ረጅም ጊዜ ወስዶ መሥራትን የሚጠይቅ ሲሆን በስልጠና ቆይታችን የቀሰምነውን እውቀትና ክህሎት መመዘን የሚያስችል ና አቅም ገንብተን ወደ ስራ እንድንገባ የሚረዳን ሲሆን የስነ-ምግባር መመዘኛውም የህዝብ አገልጋይነት ስሜት እንዲኖረን የሚያስችል ነው።
አስተያየት ሰጭው ጨምረውም የዳኝነት ና የዓቃቢ ህግነት የሙያ ስነ-ምግባር ለሙያው ወሳኝ በመሆኑ መመዘኛ መኖሩ ነገ ወደስራ ስንገባ ለምናገለግለው ማህበረሰብ በታማኝነት፣ በእውነት ና በቅንነት ላይ የተመሠረተ የአሰራር ስርዓት እንድንከተል የሚረዳን ነው ብለዋል።
ምዘናው የሙያ ስነ-ምግባርን ጨምሮ ፣ የወንጀል ሥነ-ስርአት፣የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ፣የውሳኔ አፈጻጸምና የአመራር ክህሎት የሚሉ ይዘቶችን ያካተተ ነው።
የኢንስቲትዩቱ ተወካይ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ታደሰ እንደገለጹት ሰልጣኞቹ ከዚህ ምዘና በኋላ በረዳት ዳኝነት እና አቃቢያነ ህግነት በመመደብ ወደ ተግባራዊ ልምምድ ስራ የሚገቡ መሆኑን ተናግረዋል።





All reactions:
111111
