የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት የ2017በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት በ2017በጀት ዓመት በክልሉ ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 299/2017 እንደገና የተቋቋመ ሲሆን የለውጥ ሥራዎችን አፈጻጸም በማካተት “ለፍትህና ለህግ የልህቀት ማዕከልነት እንተጋለን”! በሚል መሪ ሃሳብ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ አካሄደ።

የኢንስቲትዩቱ የዕቅድ አፈፃፀም በዕቅድ ዴይሬክቶሬት በኩል ከቀረበ በኋላ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጥያቄዎችንና አስተያየቶች ን በማቅረብ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ገምግሟል ።በመድረኩ በበጀት ዓመቱ መሠረታዊ የሚባሉ የሪፎርም ስራዎች የተጀመሩበት መሆኑም ተመላክቷል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ደሴ ጥላሁን(ዶ/ር) እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ከሁሉም በላይ ተቋሙ ለበርካታ ዓመታት የነበረበትን መዋቅራዊ እና የፋሲሊቲ እንዲሁም አጠቃላይ የተቋሙ ግንባታ ችግሮች እንዳሉ መንግስት በውል እንዲገነዘባቸው በማድረግ እና በክልሉ የተጀመረው የዳኝነት እና የፍትህ አካላት ትራንስፎርሜሽን ስራዎች አካል ሆኖ ተቋማዊ ለውጦች የተጀመሩበት በጀት ዓመት በመሆኑ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው ብለዋል።

በመሆኑም በአዲሱ ህግ የመጣውን የአደረጃጀት እና የተልዕኮ ለውጦችን መነሻ ያደረጉ የተቋም የሪፎርም ስራዎች ተጀምረዋል።

ኢንስቲትዩቱ በ2017በጀት ዓመት የ16ኛ ዙር የቅድመ ስራ ሰልጣኞች ወደ ዳኝነትና ፍትህ ስርዓቱ እንዲቀላቀሉ ያደረገ ሲሆን በተለይም የ17ኛ ዙር ቅድመ ስራ ስልጠናን ቦርዱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በአዲስ እሳቤ የስልጠና ይዘቶችን በመከለስ፣ የሙያ ምርጫቸውን አስቀድሞ በመለየት እና የተግባር ልምምድ እንዲካሄድ በማድረግ ስልጠናውን በውጤታማነት መምራት የተቻለበት መሆኑን በግምገማው ተጠቁሟል።

የጥናትና ምርምር ስራዎችም በተያዘላቸው እቅድ መሠረት እየተሰሩ ሲሆን በቀጣይ በትኩረት ሊታረሙ የሚገባቸው ውስንነቶችን በመገምገም ተለይተዋል። በአጠቃላይ የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም ሰፊ ትምህርት የሚወሰድበት ሲሆን በአፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ያላቸው ዳይሬክተሮችና ፈጻሚዎች በመድረኩ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በዚሁ መድረክ የ2018በጀት ዓመት የኢንስቲትዩቱ እቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ዕቅዱ ከክልሉ የዳኝነት እና የፍትህ ዘርፍ ዕቅድ ጋር በተጣጣመ መልኩ የታቀደ መሆኑን አስተያየታቸውን የሠጡ ተሳታፊዎች ገልጸው አያይዘውም አንዳንድ የእቅዱ ዓላማዎችና ተግባራት ሊሳኩ የሚችሉ ናቸው ወይ? በቂበጀት ተመድቧል ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመድረኩ የኢንስቲትዩቱን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ አበራን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኝ ና ተመራማሪዎች ፣ዳይሬክተሮች ሁሉም ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን ዋና ዳይሬክተሩ ደሴ ጥላሁን

(ዶ/ር) ማጠቃለያ ሲሰጡ ዕቅዱን በውጤታማነት ለመፈጸም የሰውኅይሉ በትጋት ፣በውጤታማነት እና በተስተካከለ ስነምግባር መስራት የሚገባው መሆኑን ጠቁመው የ2018 በጀት ዓመት ለተቋማችን የፋሲሊቲ እና አቅም ግንባታ መሠረት ለመጣል ወሳኝ በጀት ዓመት ነው ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረውም የክልሉ መንግስት ለዕቅዱ ማስፈጸሚያ ከመደበው በጀት በተጨማሪ ኢንስቲትዩቱ ለቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ እንዲሆን ከረጅ ድርጅቶች ተጨማሪ ኅብት ለማፈላለግ ፣የቀረጸውን ፕሮጀክት ተግባራዊ በማድረግና ሃብቱን በውጤታማነት በመምራት ዕቅዳችንን ለማሣካት ርብርብ እናደርጋለን ብለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top