የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት የራሱን የመረጃ ትስስር መተግበሪያ ድህረ-ገጽ የማልማት ሂደት ያለበትን ደረጃ ገመገመ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት የራሱን የመረጃ ትስስር መተግበሪያ ድህረ-ገጽ የማልማት ሂደት ያለበትን ደረጃ ገመገመ

የአብክመ የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት በክልሉ ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 299/2017 እንደገና የተቋቋመ ሲሆን በህጉ የተሰጡትን የቆዩ እና አዳዲስ ተልዕኮዎች ለመፈፀም ዌብ ሳይት ማልማት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ በክልሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሙሉ ትብብር ዌብ ሳይት የማስለማት ስራው ተጠናቆ አገልግሎት ለማስጀመር የቢሮው የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ስራው የሚገኝበትን ሪፖርት ለኢንስቲትዩቱ ስራ አመራር አቅርበው ውይይትና ግምገማ ተደርጓል፡፡

በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ እየለማ የሚገኘው የኢንስቲትዩት ድህረ-ገፅ ጥራቱንና አገልግሎቱ የሚገኝበትን የቴክኖሎጂ ስታንዳርድ በሚያሟላ አግባብ የተዘጋጀ እና በፋይዳ ደረጃ የኢንስቲትዩቱን ተልዕኮዎች ተደራሽ በማድረግና ከአቻ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የዌብና አፕሊኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደጀኔ ሃብቴ ገልፀዋል፡፡

በክልሉ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የዌብ ልማት ባለሙያ ወ/ሪት አሰፉ ጀምበር መተግበሪያውን በማስተዋወቅ ሂደት ተጨማሪ ማብራሪያ ለኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም በለማው ድህረ-ገፅ ላይ የተሰጡትን ሃሳቦች በማካተት እና ስልጠናዎችን በመስጠት ኢንስቲትዩቱ ሙሉ በሙሉ ድህረ-ገፁን የሚያስተዳድርበትን ሁኔታ የሚፈጥሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ደሴ ጥላሁን (ዶ/ር) በውይይቱ ተገኝተው በሰጡት አስተያየት ድህረ-ገፅ ማልማትና መጠቀም የተቋማችንን ገጽታ ለመገንባት ትልቅ እርምጃ መሆኑንና በተለይም የተቋሙን ተልዕኮዎች የሚያግዙ መረጃዎችን በመጫን፤ እና ከዘርፉ አቻ ተቋማት ጋር ለምናደርገው የትብብር ስራ ወሳኝ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ጠቁመው በውይይቱ ወቅት የተሰጡ አስተያየቶችን የማካተት ስራው እንደተጠናቀቀ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት የለማውን ድህረ-ገፅ ርክክብ በማድረግ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top